| እግር ኳስእግርኳስ

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል

22ኛው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሃግብሮቹን ዛሬ የሚያከናውን ሲሆን በሶዶ ስታድየም ወላይታ ዲቻ ከ ሲዳማ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠብቋል፡፡
በባለፈው አመት የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ የተከናወነ ሲሆን አዲሱ የሊጉ አብይ ኮሚቴ በመጀመሪያው ሳምንት የሚደረገው ይህንን መርሃግብር ያለምንም ስጋት እንደሚጠናቀቅ ከሚሚለከታቸው አካላት ጋር አስቀድሞ ውይይት አድርጓል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ሁሉም በተመሳሳይ 9 ሰዓት የሚከናዎኑ ሲሆን በአዲስ አበባ ስታድየም የሊጉ አዲስ ቡድን ሰበታ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን ይገጥማል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ሻምፒዮን የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዝዋይ ላይ በሼር ኢትዮጵያ ሜዳ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ይጫወታል፡፡
የፕሪሚየርሊጉ የወቅቱ ሻምፒዮን መቀለ 70 እንነደርታ ደግሞ ሌላኛውን አዲስ አዳጊ ቡድን ሃዲያ ሆሳዕና የሚገጥምበት ጨዋታ ሲጠበቅ በአዳማ አበበ ቢኪላ ስታድየም አዳማ ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር ይገናኛሉ፡፡
የአዲሴ ካሳው ሃዋሳ ከተማ ደግሞ የስምዖን አባዩን ድሬድዋ ይጋብዛል፡፡

የፕሪሚየርሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ነገም ሲቀጥሉ ጅማ አባጅፋር ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም የካሳዬ አራጌው ኢትዮጵያ ቡና ወደ ትግራይ አምርቶ ከስሁል ሽረ ይጫወታል፡፡

Similar Posts