| እግር ኳስእግርኳስዜና

ፋሲል ከነማ የአሸናፊዎች አሸናፊ የዋንጫ ባለቤት ሆነ::

የኢትዯጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው መቀለ 70 እንደርታ ከጥሎ ማለፉ የዋንጫ ባለቤት ፋሲል ከነማ ጋር የተገናኙበት የአሸናፊዎች አሸናፊ የዋንጫ ጨዋታ ሲደረግ ፋሲል አንድ ለምንም ረቷል::

በአዲስ አበባ ስታድየም የተደረገው ይህ መርሃግብር በሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች ልዩ ድባብ ቢኖረው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴው ብዙም ሳቢ አልነበረም::

ፋሲል ከነማ የመስመር ተጨዋቹን አብዱሮህማን ሙባረክ በጉድት ምክንያት ሳይዝ የገባ ሲሆን የገብረመድህን ሃይሌው መቀለ 70 እንደርታም አዲስ ፈራሚው ኦኪኪ አፎላቢና አምበሉ ሚካኤል ደስታን አልተጠቀመም::

በተለይም የመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታው እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ ከሚደረጉ ሙከራዎች ውጭ አካላዊ ንክኪ የበዛበትንና መሃል ሜዳው ላይ የተገደበ ነበር

የፋሲሉ እንየው ካሳሁን ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ተቀይሮ የገባው ሰይድ ሀሰን 75ኛው ደቂቃ ላይ በግራ በኩል ያሻማውን ሙጅብ ቃሲም ወደ ግብንት ቀይሮ ክለቡን ባለድል አድርጏል::

ከግቧ መቆጠር በሗላ የተሻለ እንቅስቃሴ በፈጣን መልሶ ማጥቃት በሁለቱም በኩል ቢታይም ኳስን ከመረብ የሚያገናኝ ተጨዋች ጠፍቷል::

ጨዋታው በዚህ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የፕሪሚየር ሊጉ መርሃግብር ከመጀመሩ በፊት በፋሲል ከነማ አሰልጣኝነት የመጀመሪያ ዋንጫቸውን አግኝተዋል::

ከዚህ አመት ጀምሮ የጥሎ ማለፍ ውድድር እንደማይኖር አስቀድሞ መታወቁን ተከትሎ ፋሲል ከነማ የመጨረሻው የአሸናፊዎች አሸናፊ ለመሆን በቅቷል::

Similar Posts