አትሌቲክስ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው 3 የፍፃሜ ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ

ኳታር ዶሃ ላይ በመካሄድ ላይ በሚገኘው እና 9ኛ ቀኑን በያዘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ምሽት ከ02፡55 ጀምሮ በሴቶች የ1500ሜትር እና 5000ሜትር በወንዶች ደግሞ የማራቶን ፍፃሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡

በሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያዎቿን በብቃት አልፋ ለፍፃሜው የደረሰችው ብቸኛ ኢትጵያዊት አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በሻምፒዮናው ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያ ታስመዘግባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያውን ያለፉት ፀሀይ ገመቹ፣ ሃዊ ፈይሳ እና ፋንቱ ወርቁ ኢትዮጵያን ወክለው በፍፃሜው ብርቱ ፉክክር የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

ዛሬ እኩለ ሌሊት ሊሆን 1 ደቂቃ ሲቀረው የሚደረገው ብቸኛው ኢትዮጵያውያን ወንዶች የሚሳተፉበት ውድድር ማራቶን ሲሆን ሞስነት ገረመው፣ ሌሊሳ ዴሲሳ እንዲሁም ሙሌ ዋሲሁን ይሳተፋሉ፡፡

Similar Posts