አትሌቲክስ

በሴቶች 5000 ሜትር ኬንያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀቁ

ዛሬ በተካሄደው የሴቶች 5000ሜትር ፍፃሜ ፀሀይ ገመቹ፣ ሃዊ ፈይሳ እና ፋንቱ ወርቁ ኢትዮጵያን ወክለው በፍፃሜው ብርቱ ፉክክር ቢያደርጉም በኬንያውያን አትሌቶች ብልጫ ተወስዶባቸው ውጤት ሳይቀናቸው ቀርቷል፡፡

ርቀቱን ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ 14፡26.72 በሆነ ሰዓት በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ ሌላዋ የሀገሯ ልጅ ማረጋሬት ቼሊሞ 14፡27.49 በሆነ ሰዓት 2ኛ ደረጃ ሆናለች፡፡ ጀርመናዊቷ ኮንስታንዝ ክሎስተርሃልፈን 14፡28.43 በሆነ ሰዓት 3ኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

ፀሀይ ገመቹ 4ኛ፣ ፋንቱ ወርቁ 6ኛ እንዲሁም ሃዊ ፈይሳ 8ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

Similar Posts