አትሌቲክስ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የወንዶች 1500ሜ ግማሽ ፍፃሜ ሳያልፉ ቀሩ

ዛሬ በተደረገው የወንዶች 1500ሜትር ግማሽ ፍፃሜ የተሳተፉት ሁለቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ፍፃሜው ማለፍ አልቻሉም፡፡ በመጀመሪያው ምድብ የተሳተፈው ታደሰ ለሚ በ3፡38.79 በሆነ ሰዓት 12ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ በሁለተኛው ምድብ ማጣሪያውን ያደረገው ሳሙኤል ተፈራ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 200 ሜትር ገደማ ሲቀረው አቋርጦ ወጥቷል፡፡

በውጤቱ መሰረትም በመዝጊያው ቀን በሚካሄደው የ1500ሜትር ወንዶች የፍፃሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያን የሚወክል አትሌት እንደማይኖር ተረጋግጧል

Similar Posts