አትሌቲክስ

በ3000ሜትር መሰናክል ለሜቻ ግርማ 2ኛ ሆኖ አጠናቀቀ

ዛሬ በተደረገው የ3000ሜ ፍፃሜ ጌትነት ዋሌ፣ ለሜቻ ግርማ እንዲሁም ጫላ በዮ የተሳተፉ ሲሆን ለሜቻ ውድድሩን 8፡01.36 በሆነ ሰዓት በ1 ማይክሮ ሰኮንድ ብቻ በኬንያዊው ኪፕሪቶ ተበልጦ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

ጌትነት ዋሌ 8፡05.21 በሆነ ሰዓት ሞሮኮዋዊውን ኢል ባካሊን ተከትሎ 4ኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ በፍፃሜው የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌትጫላ በዮ ውድድሩን ለማጠናቀቅ  1 ዙር ሲቀረው አቋርጦ ወጥቷል፡፡

በውጤቱ መሰረትም ኢትዮጵያ 3ኛ የብር ሜዳልያ አስመዝግባለች፡፡ በሜዳልያ ሰንጠረዡም 6ኛ ደረጃን ይዛለች

Similar Posts