ዛሬ ሐሙስ መስከረም 22 በተደረገ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወንዶች 1500ሜትር የመጀመሪያ ማጣሪያ ሳሙዔል ተፈራ 3፡37.82 በሆነ ሰዓት ከምድቡ 7ኛ ሆኖ ቢያጠናቅቅም የተሻለ ሰዓት በማስመዝገቡ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችሏል፡፡
በምድብ ሁለት በተደረገው ማጣሪያ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ታደሰ ለሚ በውድድሩ ላይ ጥሩ አቅም ቢታይበትም የመጨረሻው ዙር ላይ መስመር ለመቀየር ጥረት በሚያደርግበት ወቅት እገሩ የሌላ አትሌትን ጉልበት በመንካቱ ተደናቅፎ ወድቋል፡፡ ታደሰ ከወደቀበት በመነሳት ለመፎካከር ቢሞክርም አትሌቶች ወደ ውድድሩ ማገባደጃ ላይ በመድረሳቸው ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
በማጣሪያው ላይ የአወጣጥ ችግር በሁለቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ላይ የተስተዋለ ሲሆን ሳሙኤል ተፈራም እንዲሁ በተመሳሳይ መስመሩን ቀይሮ ለመውጣት ሲቸገር ተስተውሏል፡፡