አትሌቲክስ

በ1500ሜ የሴቶች ማጣሪያ ለምለም ሃይሉ እና ጉዳፍ ፀጋይ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፉ

በ1500ሜ ሴቶች ማጣሪያ ለምለም ሃይሉ ፣ጉዳፍ ፀጋይ እና አክሱማዊት አምባዬ የተሳተፉ ሲሆን ለምለም ሃይሉ ከምድብ 1 በ4:05.61 7ኛ ደረጃን ይዛ በማጣሪያው የተሻለ ሰዓት ተይዞላት ወደ ግማሽ ፍፃሜ ስታልፍ ጉዳፍ ፀጋይ ከ ምድብ 2 4:08.39 በሆነ ሰዓት 3ኛ ደረጃን በመያዝ በቀጥታ ማለፍ ስትችል ከምድብ 3 አክሱማዊት አምባዬ በ4:08.56 9ኛ ደረጃን በመያዟ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።
ግማሽ ፍፃሜው ነገ መስከረም 22፣2012 ዓ.ም ምሽት 05:00 ላይ የሚካሄድ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 24 ፣2012 ፍፃሜው ይካሄዳል።

Similar Posts