አትሌቲክስ

በ3000ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ፍፃሜው አልፈዋል

ዛሬ በተደረጉ የ3000ሜ ማጣሪያዎች ጌትነት ዋሌ እና ለሜቻ ግርማ ከየመድባቸው በበለይነት አጠናቀዋል፡፡ ጌትነት ዋሌ የተሳተፈበትን ምድብ 8፡12.96 በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን በሁለተኛው ምድብ የተሳተፈው ለሜቻ ግርማ ደግሞ 8፡16.64 በሆነ ሰዓት በተመሳሳይ በአንደኝነት አጠናቋል፡፡

ጫላ በዮ በበኩሉ በተሳተፈበት ምድብ 4ኛ ሆነ ያጠናቀቀ ሲሁን ባስመዘገበው የተሻለ ሰዓትም ወደ ፍፃሜ ማለፍ ችሏል፡፡ በውጤቱ መሰረትም ዓርብ ለሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር ሦስቱ አትሌቶች ኢትዮጵያን የሚወክሉ ይሆናል

Similar Posts