አትሌቲክስ

ሙክታር እድሪስ 5ሺ ሜትር ውድድርን በበላይነት አጠናቀቀ

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ በ5ሺ ሜትር በሙክታር እድሪስ አማካኝነት የተገኘ ሲሆን ሰለሞን ባረጋም ካናዳዊውን መሃመድ አህመድን በማስከተል 2ኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ 2ኛውን ብር አስገኝቷል፡፡ በ5ሺ ሜትር ማጣሪያ ላይ ልዩ ብቃት አሳይቶ የነበረው ሌላው ኢትዮጵያዊው አትሌት ጥላሁን ኃይሌ 4ኛ በመሆን አጠናቋል፡፡

“ጥሩ የቡድን ስራ ሰራን፣ ተደመርን፣ አሸነፍን እኔም ደገምኩት!! እንኳን ደስ አለን ኢትዮጵያውያን” ሲል ሙክታር በተለይም ለኢትዮላይቭስኮር ስለ ውድድሩ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

በእለቱ በተደረገው የሴቶች 3000ሜትር መሰናክል አትሌት መቅደስ አበበ ውድድሩን 9፡25.66 በሆነ ሰዓት 11ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡ ርቀቱን ኬንያዊቷ ቤትሪች ቼፕኮይች 8፡57.84 በሆነ ሰዓት በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ አሜሪካዊቷ ኤማ ኮበርን እና ጀርመናዊቷ ጌሳ ፌሊሺታስ 2ኛ እና 3ኛ በሀሞን ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት አሜሪካ በ4 ወርቅ፣ 6 ብር፣ 1 ነሐስ በድምሩ በ11 ሜዳልያ በመሰብሰብ የሜዳልያ ሰንጠረዡን ስትመራ ቻይና በ2 ወርቅ፣2 ብር፣ 2 ነሐስ በድምሩ በ6 ሜዳልያ በሁለተኝነት ትከተላለች፡፡ ጀማይካ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ከ3 እስከ 5ኛ ደረጃ ያለውን ይዘዋል፡፡

1ኛ አሜሪካ 11 ሜዳልያ (4 ወርቅ፣ 6 ብር፣ 1 ነሐስ)

2ኛ ቻይና 6 ሜዳልያ (2 ወርቅ፣ 2 ብር፣ 2 ነሐስ)

3ኛ ጀማይካ 4 ሜዳልያ (2 ወርቅ፣ 2 ብር)

4ኛ ኬንያ 3 ሜዳልያ (2 ወርቅ፣ 1 ነሐስ)

5ኛ ኢትዮጵያ 3 ሜዳልያ (1 ወርቅ፣ 2 ብር)

Similar Posts