አትሌቲክስ

በሴቶች 10ሺ ሜትር ለተሰንበት ግደይ ለሀገሯ የመጀመሪያውን ሜዳልያ አስገኘች፡፡

ዶሃ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዩና የሴቶች 10ሺ ሜትር የፍፃሜ ዳድድር ለተሰንበት ግደይ 30፡21፡23 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በሁለተኝነት በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የብር ሜዳልያ አስገኝታለች፡፡ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ30፡44.23 በሆነ ሰዓት 6ኛ ስትወጣ ነፃነት ጉደታ በበኩሏ ለማጠናቀቅ 1600ሜ ሲቀራት ውድድሩን ለማቋረጥ ተገዳለች፡፡ ውድድሩን ሲፋን ሀሰን በ30.17.62 በሆነ ሰዓት በመሪነት ስታጠናቅቅ ኬንያዊቷ አግነስ ቲሮፕ በ30.25.20 በሆነ ሰዓት 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

Similar Posts