አትሌቲክስ

በ36ኛውን የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የ10ኪ.ሜ. የአዋቂዎች ውድድር ዴራ ዲዳ እና ሞገስ ጥዑማይ አሸነፉ

ሲጠበቅ በነበረው የ10 ኪ.ሜ. አዋቂ ሴቶችን ውድድርን አትሌት ደራ ዲዳ ከኦሮሚያ በ35:49.32 አሸንፋለች፡፡ ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ ዘነቡ ፍቃዱ ሶስተኛ ናቸው፡፡

ከባድ ፉክክር በታየበት የ10ኪ.ሜ. አዋቂ ወንዶች ሞገስ ጥዑማይ ከመሰቦ ሲሚንቶ በ31:15.98 ቀዳሚ ሲሆን ሰለሞን ባረጋ ሁለተኛ እና አንዷለም በልሁ ሞገስን ተከትለው ገብተዋል፡፡

በወጣት አትሌቶች የ6ኪ.ሜ. ከ20አመት በታች ሴቶች ውድድር ግርማዊት ገ/እግዚአብሄር በ 21:25.92 ቀዳሚ ስትሆን አለሚቱ ታኩ እና ፅጌ ገ/ሰላማ ተከታዮቹን ደረጃዎች በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

በ8 ኪ. ሜ. ወጣት ወንዶች አትሌት ንብረት መላክ በ25:01:41 አሸናፊ አሸናፊ ሲሆን ፀጋዬ ኪዳኑ እና ሚልኬሳ መንገሻ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነዋል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ በወጣቶች ከ1ኛ እስከ 6ኛ ፥ እንዲሁም በአዋቂዎች ከ1ኛ እስከ 5ኛ ሆነው ያጠናቀቁ አትሌቶች መጋቢት 21 በዴንማርክ በሚካሔደው የአለም የሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ በቀጥታ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

ምስል: የኢ.አ.ፌ ይፋዊ ፌስቡክ ገፅ

Similar Posts