እግርኳስ

የሀዘን መግለጫ | ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሃግብር ባህርዳር ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ተመልክተው ሲመለሱ የነበሩ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

በደረሰው አደጋ ሁለት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው የህክምና ክትትል ላይ እንደሚገኙ ክለቡ አሳውቋል።

አደጋውን አስመልክቶ ፋሲል ከነማ የሚከተለውን የሃዘን መግለጫ አስተላልፏል

ኢትዮ ላይቭ ስኮር በደጋፊዎቹ ህልፈት የተሰማትን ሀዘን እየገለፀች፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናቱን ትመኛለች። እንዲሁም በህክምና ላይ የሚገኙትም ፈጣሪ ምህረቱን እንዲያደርግላቸው ትመኛለች።

ነፍስ ይማር

Similar Posts