እግርኳስ

የመጨረሻው ሳምንት ጨዋታዎች  ተደርገዋል፣ ዙሩ ሊጠናቀቅ አንድ ጨዋታን ይጠብቃል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዲቪዚዮን አራት ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል።

የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻው ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሲካሄዱም ሶስቱ ግጥሚያዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።

የሊጉ መሪ አቃቂ ክፍለ ከተማ ወደ ጎንደር ተጉዞ ከፋሲል ከነማ ጋር 0ለ0 ተለያይቷል። መቀለ 70 እንደርታ ሻሸመኔን 2ለ1 አሸንፏል፣ ውጤቱ አሸናፊው መቀለን ነጥቡን እንዲያሻሽል አድርጎታል።

አዲስ አበባ ስቴዲየም ላይ ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ  ቦሌ ክፍለ ከተማን ከቂርቆስ ጋር ያገናኘው ጨዋታ ያለምንም ጎል ተጠናቋል። ልደታ ክፍለ ከተማ  1ለ0  ሲመራ ቆይቶ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሰባት ደቂቃዎች ሲቀር የተቆጠረበት ጎል ከንፋስ ስልክ ጋር 1ለ1 እንዲለያይ አድርጎታል።

የኢትዮጵያ ሴቶች የሁለተኛው ዲቪዚዮን ውድድርን ስምንት ክለቦች ሲወዳደሩበት፣ የአንደኛው ዙር  ሊጠናቀቅ  ፋሲል ከመቀለ የሚያደርጉት አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ይቀራል።

ውድድሩን አቃቂ ክፍለ ከተማ በ17 ነጥብ ሲመራ፣ መቀለ70 እንደርታ በ15 ሁለተኛ ነው፣ ሻሸመኔ እና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በግብ ክፍያ ተበላልጠው በእኩል 11 ነጥብ ተከታታዩን ደረጃ ይዘዋል።

Similar Posts