እግርኳስ

በአንደኛው ዲቪዚዮን ጌዲኦ ዲላ ደረጃውን ሲያሻሽል ቅዱስ ጊዮርጊስም አሸንፏል

በአንደኛው ዲቪዚዮን ጌዲኦ ዲላ ደረጃውን ሲያሻሽል ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸንፏል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የስምንተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ፣ ዕሁድ እና ሰኞ ተደርገዋል።

ቅዳሜ ዕለት በተደረገው ብቸኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኤሌክትሪክን 3ለ0 አሸንፏል። በሊጉ ሁለተኛ ድሉ መሆኑ ነው፣ነጥቡንም ሰባት አድርሷል።

የፕሪምየር ሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ አሰላ ተጉዞ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚን 1ለ0 አሸንፏል፣ ውጤቱም መሪነቱንም እንዲያጠናክር አድርጎታል።

በቅርብ ርቀት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አዳማ ከተማም አርባምንጭን 3ለ1 ረቷል። መከላከያ ጃንሜዳ በሚገኘው ሜዳው ጥረት ኮርፖሬትን አስተናግዶ 2ለ0 አሸንፏል። ሀዋሳ ከተማም ድሬደዋን 2ለ0 ያሸነፈበት ሌላኛው የዚህ ሳምንት ጨዋታ ነበር።

በዕለተ ሰኞ አዲስ አበባ ስቴዲየም ላይ በተደረገ፣ ብቸኛ ጨዋታ ጌዲኦ ዲላ አዲስ አበባን 1ለ0 አሸንፏል።

አሸናፊው ዲላ ደረጃውን አሻሽሏል፣ ከጨዋታው በፊት ሁለቱ ቡድኖች በእኩል 13 ነጥብ ላይ ይገኙ ነበር።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ22 ነጥብ ሲመራ አዳማ በ20 ነጥብ ሁለተኛ ነው።መከላከያ በ18 ሶስተኛ ላይ ተቀምጧል።

Similar Posts