እግርኳስ

ሽመልስ በቀለ የግብጹ መስር አልማቅሳ ክለብን ተቀላቀለ

የቀድሞ የሀዋሳ ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው ሽመልስ በቀለ ወደሊቢያ አምርቶ ብዙም ሳይቆይ ወደግብፅ በማቅናት ለፔትሮጄት ሲጫወት ቆይቷል፡፡

ሽመልስ በፔትሮጄት 4 ዓመታትን ያሳለፈ ሲሆን ቡድኑን በአምበልነት በመምራት እንዲሁም ግቦችን በማስቆጠር ግልጋሎቱን ሰጥቷል፡፡

ሽመልስ ዛሬ ባገኘነው መረጃ መሰረት ከፔትሮጄት ወደ መስር አልማቅሳ የተዛወረ ሲሆን ከክለቡ ጋር የሚያቆየውን የሶስት ዓመት ተኩል ስምምነት ስለመፈራረሙ ተሰምቷል።

ዘንድሮ እየተካሄደ በሚገኘው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ ዛማሌክ የሊጉን ሰንጠረዥ በ41 ነጥብ ሲመራ፣ ሽመልስ በቀለን ወደ ክለቡ ያዛወረው መስር አልመቅሳ በ27 ነጥቦች 4ኛ ደረጃ ላይ የያዘ ሲሆን ፔትሮጄት በበኩሉ በ15 ነጥቦች የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ይገኛል፡፡

Similar Posts