እግርኳስ

በሰባተኛው ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ ንግድ ባንክ አሸነፈ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የአንደኛው ዲቪዚዮን የሰባተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተደረገ አንድ ጨዋታ ተጀምሯል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከአምናው የሁለተኛው ዲቪዚዮን ሻምፒዮን ጥረት ኮርፖሬት ጋር ያገናኘው ጨዋታ በንግድ ባንክ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ህይወት ዳንጊሶ በፍፁም ቅጣት ምት ያስቆረችው ግብ ንግድ ባንክን አሸናፊ አድርጎታል። ንግድ ባንኮች ነገ (ዕሁድ) አዳማ ከድሬደዋ ጋር የሚያደርጉት  ጨዋታ እስከሚከናወን የመሪነት ቦታቸውን ይዘዋል።

የሰባተኛው ሳምንት ቀሪዎቹ አምስት ጨዋታዎች ዕሁድ ላይ የሚደረጉ ናቸው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ከተማ በ8 ሰዓት፣ ኤሌክትሪክ ከመከላከያ በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስቴዲየም የሚደረጉ ጨዋታዎች ሲሆኑ፣ ፣ አርባምንጭ ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ፣ ጌዲኦ ዲላ ከሀዋሳ ፣ድሬደዋ ከአዳማ 9 ሰዓት ላይ በክልል ከተሞች የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።

Similar Posts