እግርኳስ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዋና እና ምክትል ፀሃፊ ሾመ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ታህሳስ 25 ቀን 2011 ዓ.ም በአደረገው መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአዲስ መልክ በአዘጋጀው የአደረጃጀት ሪፎርም ጥናት መሠረት የሰው ሃብት አደረጃጀት ምደባ በአዲስ መልክ በአስቸኳይ እንዲጠናቀቅ ውሳኔ አስተላለፈ።

ይሄን ተግባራዊ ለማድረግ ሁለት ሹመቶችን ያካሄደ ሲሆን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊነት ዶ/ር ኢያሱ መርሃፅድቅን እንዲሁም አቶ ሰለሞን ገ/ሥላሴን በፌዴሬሽኑ ምክትል ዋና ፀሐፊነት እና በእግር ኳስ ልማት ኃላፊነት የተመደቡ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

Similar Posts