እግርኳስ

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውይይት እና የሽልማት ስነስርዓት አከናወነ

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ከሚገኙ ክለቦች ጋር በተለያዩ ስድስት ነጥቦች ላይ ተወያይቷል።

የፌዴሬሽኑ ድክመት እና ማሻሻያ፣ የማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ስፖርታዊ ጨዋነት፣ ለክለቦች ድጋፍ የማድረጊያ መንገድ በሚሉት ዙሪያ ተወያይቷል።
ክለቦቹ ያለባቸውን የማዘውተሪያ ችግር በስፋት ያነሱ ሲሆን ፌዴሬሽኑም እገዛውን እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

ከዚህ ውይይት በኃላ ፌዴሬሽኑ በ13ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ  ተሳታፊ ለነበሩ ክለቦች እና አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት እንዲሁም ለከተማዋ ስፖርት አስተዋፅኦ አድርገዋል ላላቸው ሰዎች እውቅና ሰጥቷል።
የዋንጫ አሸናፊው ኢትዮጵያ ቡና  405 ሺህ ሲሸለም፣ ለሁለተኛው ባህርዳር 270 ሺህ እንዲሁም ለደረጃ ጨዋታ አሸናፊው ጅማአባጅፋር 189ሺህ ብር ሲሰጥ ለመከላከያ 108ሺህ ተሰጥቷል። በውድድሩ ተሳታፊ ለሆኑት ለቀሪዎቹ አራት ቡድኖች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 81 ሺህ ብር ተበርክቶላቸዋል።

በተለያየ ዘርፍ ለከተማዋ ስፖርት አስተዋፅኦ አድርገዋል ተብለው እውቅና ከተሰጣቸው መካከል ኢንስትራክተር ሽፈራው እሸቱ፣ አቶ ጌታቸው አበበ፣ አሰልጣኝ ሰኢድ እና ግዛው እንዲሁም ጋዜጠኛ ኑራ ኢማም ይገኙበታል።

Similar Posts