እግርኳስ

ኢትዮጵያ ቡና የደጋፊ ማህበሩን የቦርድ ድምፅ በሁለት ጨምሯል

ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ታህሳስ 20/2011 የክለቡን 8 ኛ መደበኛ እና ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አከናውኗል።

ክለቡ በጉባኤው ባለፉት አራት አመታት የነበረውን የዝውውር እና ተያያዥ ገንዘብ ወጪ  ጉዳይ እንዲሁም ቀጣይ እቅዱ ላይ ትኩረት አድርጓል። በሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን እንዲሁም በሚገነባው ስቴዲየም እገዛ የሚረዳውን ኮሚቴም አቋቁሟል።

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ“ ኢትዮጵያ ቡና በ2012  በራሱ ሜዳ ይጫወታል፣ ሜዳው በቆርቆሮ ታጥሮም  ቢሆን በሜዳው ይጫወታል፣ ያለፈው ዓመት የ2010 የሜዳ ገቢ ምንም አልተሰጠንም፣ አዲስ አመራርም እጃችን ላይ ምንም የለም ብለውናል ” ብለዋል።

ጉባኤው የክለቡን የደጋፊ ማህበር ድምፅ ከሁለት ሰው ወደ አራት ለመጨመር ከስምምነት ላይ ደርሷል። በጉባኤው የደጋፊ ማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ክፍሌ አማረ “መጨመሩ ጥሩ ቢሆንም ካለው የደጋፊ ብዛት አንፃር የውሳኔ ሰጪነት ድምፅ ላይ አናሳ ነው ” ሲል ሀሳቡን ሰንዝሯል፣ በዚህ ነጥብ ላይ ከተወያዩም በኋላ ቀድሞ በቀረበው ሀሳብ ተስማምተዋል።

ክለቡ ከ2006 እስከ 2010 የነበረውን የገንዘብ አወጣጥ በሪፖርቱ በዚህ መልኩ ተነግሯል

2006

ደሞዝ_3.1 ሚሊየን
የስራ ግብር _ 1.1 ሚሊየን
የጡረታ _ 403 ሺህ ብር

2007

ደሞዝ_ 3.7 ሚሊየን
የስራ ግብር _ 1.3 ሚሊየን
የጡረታ 417 ሺህ

2008

ደሞዝ 11.2 ሚሊየን
የስራ ግብር 2.5 ሚሊየን
ጡረታ 700 ሺህ

2009

ደሞዝ 18 ሚሊየን
የስራ ግብር 5.3 ሚሊየን
ጡረታ 241 ሺህ

2010

ደሞዝ 30,244,000
የስራ ግብር 8.4 ሚሊየን
የጡረታ 3.7 ሚሊየን

Similar Posts