እግርኳስ

በሴቶች 2ኛ ዲቪዚዮን አቃቂ መሪነቱን አጠናከረ

ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ዲቪዚዮን የአምስተኛው ሳምንት ጨዋታዎች በዚህ ቀን ተደርገው ተጠናቀዋል።

ረቡዕ ዕለት ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ፣ ሻሸመኔ እና ፋሲል ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። ሻሸመኔ ቦሌ ክፍለከተማን 1ለ0 በማሸነፉ ነጥቡን ወደ 10 ከፍ አድርጓል፣ሁለተኛ ላይም ይገኛል። ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማን በሜዳው ያስተናገደው ፋሲል ከነማ 3ለ2 አሸንፏል።

ሀሙስ ከተደረጉት ሁለት ጨዋታዎች መካከል የውድድሩ መሪ አቃቂ ቂርቆስን 2ለ0 ረቷል። ውጤቱ አሸናፊው አቃቂን መሪነቱን እንዲያጠናክር ሲያደርገው ቂርቆስን ደግሞ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት አካባቢ የመቀመጥ ዕድሉን አሳጥቶታል።

መቀለ ልደታን 3ለ1 አሸንፏል፣ ዘንድሮ አስከፊ አካሄድን እያደረ የሚገኘው ልደታ በተለይም ከሜዳው ውጪ በሰፊ ግብ ልዩነት መሸነፍ ተደጋግሞበታል፣ በሻሸመኔም በተመሳሳይ ውጤት መሸነፉ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግን አቃቂ ክፍለ ከተማ በ13 ነጥብ እየመራ ይገኛል። ሻሸመኔ በ10 ሲከተል መቀለ እና ፋሲል በ 9 እና 8 ነጥቦች ተከታታይ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የዚሁ ዲቪዚዮን ቀጣይ የስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች የፕሮግራም ማስተካከያ ካልተደረገባቸው በስተቀር በቀጣይ ረቡዕ እና ሀሙስ መሆኑን የወጣላቸው መርሃ ግብር ያሳያል

Similar Posts