እግርኳስ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን የአሰራር የአደረጃጀት እና የአፈፃፀም ችግሮችን ለመቅረፍ ሲከናወን የነበረው የሪፎርም ጥናት ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን የአሰራር የአደረጃጀት እና የአፈፃፀም ችግሮችን ለመቅረፍ ሲከናወን የነበረው የሪፎርም ጥናት ተጠናቀቀ።

የሪፎርም ጥናቱ መጠናቀቅን አስመልክቶ ፌዴሬሽኑ  በጥናት ዝግጅቱ ላይ ለተሳተፉ አባላት ዛሬ ህዳር 29፣ 2011ዓ.ም በካፒታል ሆቴል የዕውቅና እና የምስጋና መድረክ አዘጋጅቷል።

አራት ወራትን የፈጀው እና የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑን መስረታዊ ችግሮች ይቀርፋል ተብሎ የተጀመረው ጥናቱ 10 ዓባላትን በመያዝ የመጀመሪያውን 45 ቀናት በበሻሌ ሆቴል ማረፊያውን በማድረግ  ዋና ዋና ተግባራትን ከውኗል የጥናቶቹንም ዘርፎች ለይቷል።

6ቱ ዋና ዋና የጥናቱ ዘርፎች፡-

1 ተቋማዊ ብቃት
2 ልማት
3 የሊግ ተግባራት
4 ሃብት አሰባሰብ
5 ስፖርታዊ ጨዋት
6 የፋይናንስ አጠቃቀም ሲሆኑ

ከላይ በተዘረዘሩት ዋና ዋና ዘርፎች ዙሪያ የጥናት ቡድኑ በተለያየ ቡድን በመከፋፍል ጥናቱን አካሂዷል።

ጥናቱ ሲጠናቀቅ ዋና ዋና በመባል በተለዮትት ዝርፎች ላይ ያደረገውን በባለ 500 ገፅ ጥራዝ  ይፋ አድርጓል።

ዋና ዋና መንስኤዎችዋን ከነመፍትሄያቸው ጭምር የያዘው ይህ ጥራዝ በውስጡ የማስፈፀሚያ መተገብሪያ ሰነዶችንም ጨምሮ ይዟል።

በጥናቱ ወቅት የተጠቀሙባቸው ከ1000 በላይ ጥሬ የወረቀት ሰነዶችም መቀመጣቸው ታውቋል

በጥናት ቡድኑ ላይ የተሳተፉት

አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ /ሰብሳቢ/

ወ/ሮ መስከረም ታደሰ
ወ/ሮ መሰረት በላይሁን
ዶ/ር ተፈራ ታደሰ
ዶ/ር አመንሲሳ ከበደ
ዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ
አቶ ሳሙኤል ስለሺ
አቶ ገዛኸኝ ወልዴ
አቶ ኃይለእግዚያብሔር አድሃኖም
አቶ አንበሴ መገርሳ
አቶ ተሾመ ታደሰ ናቸው

አቶ ኢሳያስ ጅራ የሰነድ ርክክቡን አስመልክቶ አንዳንድ ነጥቦችን አንስተዋል
“ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በድርጊት መርሃግብሩ መሰርት ወደ ተግባር እንደምንገባ አሳውቃለው፣
ተቋሙን የማደራጀት ስራ ቁልፍ ስራችን ይሆናል።” ብለዋል

በተጨማሪም በጥናቱ ላይ የተሳተፉ ባለሞያዎችን ያመሰገኑ ሲሆን ለጥናቱ ተግባራዊነት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

Similar Posts