አትሌቲክስ

የአቡዳቢ ማራቶን የመክፈቻ ውድድር በኢትዪጵያውያን እና ኬኒያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቀቀ

የአቡዳቢ ማራቶን የመክፈቻ ውድድር በኢትዪጵያውያን እና ኬኒያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቀቀ::

ዛሬ – አርብ ህዳር 27 የመጀመሪያው የአቡ ዳቢ ውድድር ንጋት ላይ ተካሂዷል::
የአቡ ዳቢን ሙቀትን ተከትሎ በቀዝቃዛው ሌሊት በተካሄደው ውድድር በሴቶች አባብል የሻነው አሸንፉለች:: አባብል ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:20:16 ፈጅቶባታል:: ይህም ከራሷ የቀድሞ 2:33 ምርጥ ሰዓት ከ13 ደቂቃ በላይ ያሻሻለችበት ሆኗል::
ትውልደ ኬኒያዊት የባህሬኗ ኢዮንሴ ቹንባ ሁለተኛ ገለቴ ቡርቃ ሶስተኛ ሆነዋል::

ኢትዮጵያዊው ደጀኔ ደበላ ሦስተኛ ሆኖ ባጠናቀቀበት የወንዶች ማራቶን ኬኒያዊው ማሪዮስ ኪፕሰረም 2:04:04 በሆነ ሰአት አሸንፏል:: የ30 አመቱ ኪፕሰረም በተለይ ሁለተኛውን 21 ኪሜ የሮጠበት 61 ደቂቃ ፈጣን መሆኑ በብዙዎች ግርምትን ፈጥሯል:: ሌላው ኬኒያዊ አብርሀም ኪፕቱም ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል::

ሴቶች

  1. አበባበል የሻነው(ኢትዮጵያ) – 2፡20.16
  2. ኢዮንሴ ቹምባ(ባህሬን) – 2:20:54
  3. ገለቴ ቡርቃ(ኢትዮጵያ) – 2፡24.07
  4. ጫልቱ ጣፋ(ኢትዮጵያ)- 2፡25.09

ወንዶች

  1. ማሪዮ ኪፕሰረም(ኬኒያ) – 2:04:04
  2. አብርሀም ኪፕሪቱ(ኬኒያ) – 2:04:16
  3. ደጀን ደበላ ጎንፋ(ኢትዮጵያ) – 2፡07.06
Similar Posts