እግርኳስ

“አሁን ትኩረታችን ውጤቱን ለመቀየር ነው” አሰልጣኝ ስዩም ከበደ

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን እየተካፈለ የሚገኘው መከላከያ ከናይጄሪያው ኢኑጉ ሬንጀርስ ጋር የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ረቡዕ ህዳር 26/2011  ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስቴድየም ያደርጋል።

የመከላከያ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ውጤቱን ለመቀየር እንደሚጫወቱ ተናግረዋል። አሰልጣኙ 2ለ0 ስለተሸነፉበት የመጀመሪያው ጨዋታ እና ዛሬ ስለሚደረገው ጨዋታ አስተያየታቸውን ለኢትዮላይቭ ስኮር ሰጥተዋል።

“እርግጥ ተጋጣሚያችን በኳስም ጥሩ የሚባል ቡድን ነበር፣ ነገር ግን እኛም የተቻለንን አድርገናል፣ በዳኝነቱ አዝኛለሁ፣ ሰበብ ለማቅረብ ሳይሆን እነሱም አላመኑበትም።»

እንደዚህ እና መሰል ችግሮች ሊገጥማችሁ እንደሚችል አታውቁም ነበር ወይ?  ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም

“ይሄን በራሳችን የቅድመ ጨዋታ ስብሰባም ተነጋግረናል፣ ልጆቼ ሳጥኑ ውስጥ ንክኪም እንዳያደርጉ የሚመቱ ኳሶችንም ቀድመው እዛ ሳይገባ እንዲያስጥሉ አውርተን ነበር። አንዳንዴ ግን በእኛ ጥንቃቄም ብቻ የሚወሰን ነገር አይደለም፣ ይህ ከአቅም በላይ ነው። ” ሲሉ ተናግረዋል

አሰልጣኝ ስዩም ቀጥለውም በአሰላለፋቸው የተለየ ለውጥ እንደማይኖር አስታውሰው፣ ፊት መስመሩ ላይ ግን የአጥቂው ተመስገን ገ/ኪዳን በህመም አለመኖር ተከትሎ  እሱ ቦታ ላይ መጠነኛ ማስተካከያ  እንደሚያኖር ተናግረዋል።

Similar Posts