አትሌቲክስ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቫሌንሲያ ደመቁ

ልዑል ገ/ስላሴ እና አሼቴ ዲዶ የቦታውን ክብረወሰን አሻሽለዋል::

በስፔን ምስራቃዊቷ ከተማ ቫሌንሲያ የወርቅ ደረጃ ያለው የትሪንዳድ አልፎንሶ ማራቶን ዛሬ ህዳር 23/2018ዓ.ም ትካሂዷል::
ማራቶንን ለሁለተኛ ጊዜ የሮጠው ልዑል ገ/ስላሴ 2:04:30 በሆን ሰዓት አሸንፏል:: ይህም ሰዓት ስፔናዊ ያልሆኑ በስፔን የሮጡት ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል:: የ25 ዓመቱ ልዑልን ጨምሮ የመጀመሪያዎቹ ሶስት አትሌቶች ከ2:05 በታች ሮጠዋል:: እስከ ስድስተኛ ደረጃ ያሉት ደግሞ ከ2:05:30 በታች ሰዓት አስመዝግበዋል::
የልዑል ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው እና ረጅም ኪሎ ሜትር ሲመራ የነበረው ኬኒያዊ በመጨረሻ በባህሬን አትሌት አል ሀሰን አል አባሲ ተቀድሞ ሶስተኛ ወቷል::
በስቶቹ ምድብ ኢትዮጵያዊቷ እሸቴ ዲዶ የውድድሩን ሰዓት በማሻሻል አሸንፋለች:: እሸቴ የገባችበት 2:21:14 የራሷም ፈጣን ሰዓት ነው::

ከማራቶን በተጨማሪ በተካሄደው የ10ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አብርሀ ፅጌ(32:03) አሸንፉለች::

ውጤት
ወንድ

1. ልዑል ገ/ስላሴ(ኢትዮጵያ) -2:04:30
2. ኤል ሀሰን ኤል አባሲ(ባህሬን) – 2:04:43
3. ማቲው ኪሶሪዮ(ኬኒያ) – 2:04:53
4. ፀጋየ ከበደ(ኢትዮጵያ) – 2:05:20

ሴት
1. እሸቴ ዲዶ(ኢትዮጵያ) – 2:21:14
2. ሊዲያ ቼሮሜ(ኬኒያ) – 2:22:10
3. ትንቢት ወ/ገብርኤል(ኢትዮጵያ)-2:22:37
4. አበሩ መኩሪያ(ኢትዮጵያ) – 2:24:35

Similar Posts