አትሌቲክስ

በፉኩካ ማራቶን የማነ ፀገዬ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ

ዛሬ (ህዳር 23/2011ዓ.ም) በጃፓን 72ኛው የፉኩካ ማራቶን ተካሂዷል::

የወርቅ ደረጃ ባለው በውድድሩ ሰፊ የማሸነፍ ግምት አግኝቶ የነበረው ኢትዮጵያዊው የማነ ፀጋየ ሁለተኛ ሲውጣ ይሀገሬው ሰው ዩማ ሀቶሪ ውድድሩን በላይነት አጠናቋል:: በዚህ ውድድር ጃፓናዊ አትሌት ሲያሽንፍ ከ14 ዓመታት በሗላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው::

ስድስት ኢትዮጵያውያን ከዚህ በፊት በፉኩካ ማራቶን ማሸነፍ ችለዋል:: በላይነህ ዲንሳሞ(1983) የመጀመሪያው አሸናፊ ነው:: ጠና ነገሬ፣ ገዛህኝ አበራ፣ ሀይሌ ገ/ ስላሴ፣ ፀጋዬ ከበደ እና የማነ ፀጋዬ ማሸነፍ ችለዋል::
ውጤት
1. ዩማ ሀቶሪ(ጃፓን) – 2:07:27
2. የማነ ፀጋየ(ኢትዮጵያ) – 2:08:54
3. አማኑኤል መሰል(ኤርትራ) – 2:09:45

Similar Posts