እግርኳስ

ማስተካከያ

በኢትዮላይቭ ስኮር የፕሪምየር ሊጉ የተጫዋቾች ዝውውር የየክለቡ የ2011 ዓ.ም ከፍተኛ ተከፋዮች ስም ዝርዝር ማስነበባችን ይታወሳል።

በዝርዝሩ ላይ ከባህርዳር ከነማ በኩል የተጠቀሱት ስም ዝርዝር ውስጥ ማስተዋል ዳኘው ተብሎ የተገለፀው የክለቡ ተጫዋች ሳይሆን በውሉ ላይ በአስፈራሚ ቦታ ላይ የሰፈረ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

ስህተቱ የተሰራው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዝርዝር አመዘጋገብ ላይ መሆኑን እያስታወስን ለማረጋገጫ እንዲሆን ዘንድ በፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት በመገኘት በድጋሚ እንዲታይ አድርገናል።

በመሆኑም ውል ለሚዲያ ስለማይወጣ ከውሉ ላይ ወደ ወረቀት ሲገለበጥ አስፈራሚ የሚለው የውሉ ቦታ ላይ የተጠቀሰው “ማስተዋል ዳኛው” የሚለው ስም በተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ በስህተት ገብቷል።

ለተፈጠረው ስህተት በዚህ መልኩ ማስተካከያ እንዲደረግ ከታላቅ ይቅርታ ጋር እየጠየቅን በአጠቃላይ ግን የሌሎቹ ዝርዝር ላይ ስህተት አለመኖሩን ለመግለፅ እንወዳለን።

 

Similar Posts