እግርኳስ

በሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ተደረገ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የአንደኛ ዲቪዚዮን  ተስተካካይ አንድ ጨዋታ ዛሬ ተደርጓል። የመጀመሪያው ሳምንት መርሃ ግብር  የነበረው ይህ ግጥሚያ ቅ/ጊዮርጊስን ከአርባምንጭ አገናኝቷል።

ጨዋታው በአርባምንጭ የ1ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን በ43ኛው ደቂቃ ላይ  ሰርካዓለም ባሳ ያስቆጠረችው ግብ ለእንግዳው ቡድን ሶስት ነጥቡን እንዲያሳካ አድርጋዋለች።

ሁለት ቡድኖች ብቻ ሁለት ጨዋታዎችን ሲያደርጉ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ አንድ አንድ ጨዋታዎችን አድርገዋል። ሀዋሳ ከተማ በግብ ክፍያ የተሻለ፣ በመሆኑ ሊጉን እየመራ ይገኛል።

የዚህ ዲቪዚዮን የሁለተኛው ሳምንት ቀጣይ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና ዕሁድ የሚደረጉ ይሆናል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢ/ንግድ ባንክ፣ ጥረት ኮርፖሬት ከ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ፣ አዳማ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ፣ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ከ አዲስ አበባ ከተማ፣ አርባምንጭ ከጌዲኦ ዲላ ሲጫወቱ፣ መከላከያ ድሬደዋ ከተማን 3ለ2 ያሸነፈበት ሌላኛው የዚሁ ሳምንት መርሃ ግብር መሆኑ ይታወሳል።

Similar Posts