አትሌቲክስ

የቶታል ታላቁ ሩጫ ለ18ኛ ጊዜ በድምቀት ተካሄደ

መነሻውን እና መድረሻውን 6 ኪሎ አደባባይ አድርጎ ከ44,000 በላይ ተሳታፊዎችን በድምቀት ያሳተፈው ቶታል ታላቁ ሩጫ በድምቀት ተካሂዷል።

የ ዛሬ በተደረገው የታላቁ ሩጫ  በኢትዮጵያ የመጀመሪያ መርሃ ግብር  የ…..የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ሲሆን በዚህም ውድድር በወንዶች ሀጎስ ገብረህይወት በሴቶ ፎቴን ተስፋዬ አሸናፊ ሆነዋል።

አጠቃላይ ውጤት:-

በወንዶች

  1. ሀጎስ ገ/ህይወት 28:54.3 – ከርኆቦት ኢ.አትሌቲክስ
  2. ቦንሳ ዲዳ 29:03.8- አዲስ ዴቨሎፕመንት ፕሮግራም
  3. ጥላሁን ኃይሌ 29:13.7 – ከሀዋሳ ከነማ

በሴቶች

  1. ፎቴን ተስፋዬ 33:43.5 ከመሰቦ ሲሚንቶ
  2. ፀሀይ ገመቹ 33:48.8 ከኦሮሚያ ባንክ
  3. ፅጌ ገ/ሰላማ  33:52.8 ሱር ኮንስትራክሽን

በማጠናቀቅ ከዕለቱ የክብር እንግዶች ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረሳላሴ፣ አትሌት ዘረሰናይ ታደሰ ፣ አትሌት ኪፕቾጌ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል።

በወንዶች እና በሴቶች አንደኛ ሆነው ላጠናቀቁ አትሎቶች ከ ሜዲያሊያ እና የዋንጫ ሽልማት በተጨማሪ የ 100,000.00(አንድ መቶ ሺ ብር) ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በመቀጠልም ብዙ ተሳታፊዎችን በእንድ ጊዜ የሚያሳትፈው ሩጫ በ2 ተከፍሎ የተካሄደ ሲሆን አረንጓዴ ለባሾች ማለትም 10 ኪሜ ከ 1ሰዓት በታች ይጨርሳሉ ተብለው የሚጠበቁት 7000 ሯጮች ቀድመው የተለቀቁ ሲሆኑ በመቀጠል ቀይ ለባሾች 10 ኪሜ ከ1 ሰዓት በላይ የሚያጠናቅቁ ውድድርቸውን ጀምረው በድምቀት አካሂደዋል።

ለ18 ኛ ጊዜ የተካሄደው ይህ መርሃ ግብር በየአመቱ የተሳታፊ ቁጥር እንዲሁም ድምቀቱ ከአመት አመት እየጨመረ ተታፊዎቹን ማስደሰቱን ቀጥሎበታል።

እንደ ፌስቲቫል ተሳታፊዎቹን የሚያዝናናው ታለቁ ሩጫ በዘንድሮውም ውድድር ላይ በዲጄዎች የታገዘ በተለያየ ቦታ በተቀመጡ የመዝናኛ ስፍራዎች ተሳታፊዎችን በተለያዩ ጠዑመ ዜማዎች ሲያዝናኑ ተመልክተናል።

ይህም ውድድር በኢትዮጵያውያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን የቀጥታ ስርጭት በሃገር ውስጥ እና በመላው ለአለም ተሰራጭቷል።

ከዚህም በተጨማሪ የአምባሳዶሮች እና የታዋቂ አርቲስቶች ውድድር የተካሄደ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ውድድራቸውን በማጠናቀቅ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል።.

ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ! በሚል ውድድሯን ከ 1 ሰዓት በታች በአንደኝነት ያጠናቀቀችው  አምለሰት ሙጬ ስትሆን አርቲስት ፍፁም ፣ ሚካኤል ታምሬ በተለያየ ዘርፍ በውድድር ላይ በአምባሳደርነት በመቅረብ መልዕክቶቻቸውን አስተላልፈዋል።

የአርቲስቶቹን ሽልማት ያበረከተችው አንጋፋዋ አርቲስት ሃመልማል አባተ ስትሆን በወቅቱም ክብር ለእናቶች በማለት መልዕክቷን ስታስተላልፍ ተደምጣለች።

በአጠቃላይ ውድድሩ በድምቀት ተጀምሮ በድምቀት ተጠናቋል።

Similar Posts