እግርኳስ

የኢትዮጵያ እና የጋና ብሄራዊ ቡድኖች አሰልጣኞች ስለነገው ጨዋታ አስተያየታቸውን ሰጡ

ነገ እሁድ ህዳር 09፣ 2011ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ ካሜሮን ለምታዘጋጀው የ2019 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚያደርጉት የኢትዮጵያ እና የጋና ባሄራዊ ቡድኖች ዛሬ የመጨረሻ ልምምድ ሰርተዋል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞችም ስለ ጨዋታው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብረሃም መብራቱ

“ትልቅ ጨዋታ ነው፣ ትልቅ ታሪክ ለመስራት የምንዘጋጅበት ጨዋታ ነው፡፡ የጋና ቡድን ትልቅ ቡድን ነው፣ ሁሉም ተጫዋቾች በተለያዩ የአውሮፓ ሊጎች የሚጫወቱ ናቸው፣ ከቅንጅት ስራዎች በስተቀር በደንብ ዝግጁ የሆኑ ተጫዋቾች የያዘ ቡድን ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ቡድን ሳናከብድ ነገር ግን ተገቢወውን ክብር ሰጥተን በጥንቃቄ ተጫውተን ድሉን ይዘን ለመውጣት አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡”

የጋና ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኬውሲ አፒአህ

 

“ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ተጫውቻለው እውነት ለመናገር በቅርብ ያደረጓቸውንም ጨዋታዎች ምስል ተመልክቻለው፣ እናም መጥፎ ሚባል ቡድን አይደለም፣ ኳስን ተቆጣጥሮ ለመጫወት የሚሞክር መሆኑ ጥሩ ሆኖ ሳለ ካየኋቸው ምስሎች አንፃር ግን የግብ አጋጣሚዎችን መፍጠር ላይ ሲቸገር አስተውያለው፡፡”

Similar Posts