አትሌቲክስ

“ዋናዉ ዕቅዴ በአመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ዉስጥ መግባት ነበር” ሰለሞን ባረጋ

ሰለሞን ባረጋ በአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማህበር የ2018 ተስፈኛ አትሌት ዕጩ ዉስጥ መካተት ችሏል፡፡ በአመቱ የወጣቶች ዉድድር መልካም የሚባለ ዉጤትን ያስመዘገበዉ ሰለሞን ከ13 ዓመታት ወዲህ በወጣቶቹ እጅግ ፈጣን የተባለዉን ሰዓት አስመዝግቧል፡፡

ይሄንን ተከትሎ በተስፈኛ ወጣት ዕጩ ዉስጥ የገባዉ ሰለሞን ባረጋ በተለይ ለኢትዮላይቭ ስኮር እነደተናገረዉ አላማዉ የዐመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ዉስጥ መግባት ነበር፡፡

“በተለያዩ ዉድድሮች በተለይም በአፍሪካ ቻምፒዮና እና ወጣቶች አለም ሻምፒዮና በልምድ ማነስ ምክንያት ያጣኋቸዉ ድሎች ያስቆጩኛል” ብሏል፡፡ ይሁን እንጂ ሰለሞን በዚህ ምርጫ ላይ መግባቱ እንዳስደሰተዉ ተናግሯል፡፡

በአመቱ ካደረጋቸዉ ዉድድሮች በዲያመንድ ሊግ 5000ሜትር የመጨረሻ ዉድድር በብራሰልስ ያካሄደዉ በአመቱ ያስደሰተዉ ዉድድር እንደነበር ገልጿል፡፡ ሰለሞን ባረጋ በወቅቱ ርቀቱን ሲያሸንፍ የገባበት 12፡43.02 የምንግዜም 4ኛ ፈጣን ሰዓት ከ20ዓመት በታች የአለም ክብረ ወሰንም ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ሰለሞን አሰልጣኞቹ ሁልጊዜ ለፈጣን ሰዓት እንዲሮጥ ይመክሩት እንደነበር ተናግሮ በቀጣይ ዉድድሮች ለተሻለ ዉጤት እና ሰዓት ሮጣለሁ ብሏል፡፡

Similar Posts