አትሌቲክስ

ሲሳይ ለማ በስሎቬንያ መዲና በተካሄደው የማራቶን ውድድር አሸነፈ

በስሎቬንያ መዲና ጁብጃና በተካሄደው የማራቶን ውድድር በወንዶች ሲሳይ ለማ በሴቶች ደግሞ ኬንያዊቷ ጄብኬሾ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

ከውድድሩ መጀመሪያ እስከ 10ኪ.ሜ ድረስ ከፍተኛ ዝናብ የጣለ ሲሆን የ27 ዓመቱ ሲሳይ ቶላ ከ13ኛው ኪ.ሜ ጀምሮ ተነጥሎ በመውጣት 02፡04፡58 በመግባት እ.ኤ.አ 2015 በልመነህ ጌታቸው ተይዞ የነበረውን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፏል፡፡

“ክብረወሰኑን ለማሻሻል ከመጀመሪያውም ሳስብ ነበር ነገር ግን በዝናቡ ምክንያት አየሩ ከብዶኝ ነበር፣ ቢሆንም ግን ፈተና ነው፣ ፈተና ደግሞ ፅናት ይሰጠኛል”

ሲል ሲሳይ ከውድድሩ በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል፡፡

ሲሳይ በውድድሩ ያስመዘገበው ሰዓት የራሱን 2ኛ ሰዓት ሲሆን በዱባይ ማራቶን 5ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀበት 2፡04፡08 1ኛ የግል ሰዓቱ ነው፡፡

Similar Posts