አትሌቲክስ

የፍራንክፈርት ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቀቀ

እሁድ ጥቅምት 18፣ 2011 በጀርመን ፍራንክፈርት በተካሄደው ማራቶን ውድድር መስከረም አሰፋ እና ከልክሌ ገዛኸኝ በበላይነት አጠናቀቁ

ከፍተኛ ብቃት የታየበት የሴቶች ውድድር ላይ የመጀመሪያዎቹ 7 አትሌቶች 2፡23 በሆነ ሰዓት ውድድሩ ማጠናቀቅ የቻሉ ሲሆን የ33 ዓመቷ መስከረም አሰፋ 2፡20፡36 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ከዚህ በፊት እ.ኤ.አ በ2012 በመሰለች መልካሙ ተይዞ የነበረውን የውድደሩ ክብረወሰን በ25 ሰከንድ አሻሽላለች፡፡

በሴቶቹ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 6 ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት ያጠናቀቁ ሲሆን ሀፍታምነሽ ተስፋዬ እና በዳቱ ሂርፓ፣ መስከረምን በመከተል 2ኛ እና ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

በወንዶቹ በኩል በተካሄደው ውድድር ኢትጵያዊው ከልክሌ ገዛኸኝ እና 2:06:37 በሆነ ሰዓት ውድድሩን አጠናቋል፡፡ ኬንያዊው ማርቲን ኮስጌይ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 500ሜትር ያህል እስኪቀር መምራት ቢችልም ከልክሌ ገዛኸኝ የቴክኒክ ብቃቱን በመጠቀም አፈትልኮ በመውጣት ባለድል መሆን ችሏል፡፡

ወንዶች

  1. ከልክሌ ገዛህኝ (ኢትዮጵያ) – 2:06:37
  2. ማርቲን ጎስጌኝ (ኬኒያ) – 2:06:47
  3. አሌክስ ኪቤት (ኬኒያ) – 2:07:09

ሴቶች

  1. መስከረም አሰፋ (ኢትዮጵያ) – 2:20:36
  2. ሀፍታምነሽ ተስፋዬ (ኢትዮጵያ) – 2:20:47
  3. በዳቱ ሂርጳ (ኢትዮጵያ) – 2:21:32
  4. በላይነሽ ኦልጅራ (ኢትዮጵያ) – 2:21:53
  5. ደራ ዲዳ (ኢትዮጵያ) – 2:22:39
  6. ስንታየሁ ሀ/ሚካኤል (ኢትዮጵያ)- 2:22:45
Similar Posts