አትሌቲክስ

በደብሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸነፋ

በአየርላንድ ህዝባዊ በዓልን ምክንያት በማድረግ በጥቅምት ወር የመጨረሻው ዕሁድ የሚካሄደው የደብሊን ማራቶን ዛሬ ዕሁድ ጥቅምት 28/2011ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

ኢትዬጵያዊው አሰፋ በቀል የወንዶቹን ምድብ በበላይነት አጠናቋል:: አሰፋ ርቀቱን 2 ሰዓት 13 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ፈጅቶበታል፡፡
ደቡብ አፍሪካዊው ዴቪድ ማንጃ 10 ሰከንዶችን ዘግይቶ ሁለተኛ ሆኗል:: ኬኒያዊው ጆየ ኪፕቶ በ2:13:42 ሶስተኛ ሆኗል፡፡
ኢትዮጵያዊቷ መሰራ ዱቢሶ 2ሰዓት 33 ደቂቃ 48ሰከንዶች በሆነ ስዓት በሴቶቹ አሽንፋለች:: ሞቱ ገደፋ(2:34:22) እንዲሁ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

ምንጭ፡ ሌትስረን

Similar Posts