አትሌቲክስ

ታደለች በቀለ የአምስተርዳም ማራቶንን አሸነፈች

ቀነኒሳ በቀለ ዉድድሩን ሲያቋርጥ ላዉረንስ ቺሮኖ የወንዶቹን ምድብ አሸንፏል፡፡ በሆላንዷ አምስተርዳም ከተማ በየአመቱ የሚካሄደዉ የቲኤስሲ አምስተርዳም ማራቶን ትናንት ለ43ኛ ጊዜ ተካሂዷል፡፡ በሩጫዉ መጀመሪያ ላይ ቀዝቀዝ ያለ አየር እና ለሩጫ ምቹ የሆነ ንፋስ በአምስተርዳም ተስተዉሏል፡፡ በወንዶቹ ምድብ ሩጫዉን መምራት የጀመሩት አስራ አራት አትሌቶችም ተመችቷቸዉ መሮጥ ችለዋል፡፡ በዚህ ምድብ ዉስጥ የተጠበቁት ቺሮኖ እና ቀነኒሳ በቀለ ይገኙበታል፡፡ አትሌቶቹም የመጀመሪያ 5ኪ.ሜ በ14፡33 መሮጥ ችለዋል፡፡ ቀጣዩን ሲጨርሱ ደግሞ 29፡08 ይህም ከወር በፊ በበርሊን ማራቶን ኢሉድ ኪፕቾጌ የአለም ክብረ ወሰንን ሲያሻሽል 14፡29 እና 29፡01 ጋ ተቀራራቢ ነበር፡፡ በዚህ ፍጥነት መጨረስ ባይችሉም እስከ 30ኪ.ሜ ባለፈዉ አመት የቦታዉ ክብረ ወሰን ሲሻሻል የተሮጠዉን ፍጥነት መድገም ችለዋል፡፡ እስከ 35ኛዉ ኪሎ ሜትር ከመሪዎቹ ጋር የነበረዉ ቀነኒሳ በቀለ ከዚህ በኋ ግን አልቻለም፡፡ 2፡02፡30 ከሮጠ በኋላ ቀነኒሳ በቀለ አቋርጦ ወቷል፡፡

ላዉረንስ ቺሮኖ ከኢትዮጵያዉያኑ ሙሌ ዋሲሁን እና ሰለሞን ደቅሲሳ ጋር ፉክክሩን ቀጠለ፡፡ በመጨረሻም ቺሮኖ 2፡04፡06 በሆነ ጊዜ ቀዳሚ ሆኖ ገብቷል፡፡ ይህ ሰዓት ራሱ ቺሮኖ ባለፈዉ አመት(2017) ካሻሻለዉ የቦታዉ ክብረ ወሰን 2፡05፡09 የፈጠነ ሆኗል፡፡ ሙሌ ዋሲሁን በ2፡04፡37 ሁለተኛ ሲወጣ፤ ሰለሞን ደቅሲሳ በ2፡04፡40 ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

በሴቶቹ ምድብ አስከ መጨረሻዉ ጠንካራ ፉክክርን አሳይቶ ተጠናቋል፡፡ ያለፈዉ አመት አሸናፊዋ ታደለች በቀለ 2፡23፡14 በሆነ ጊዜ አሸንፋለች፡፡ ሻሾ ኢንሰርሙ (2፡23፡28) ሁለተኛ፣ አዝመራ ገብሩ(2፡23፡31) ሶስተኛ ሆነዋል፡፡ በማራቶን የመጀመሪያ ሩጫዋን ያደረገችዉ የመም ላይ ዉጤታማ አትሌቷ መሰረት ደፋር 8ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡ መሰረት ደፋር ዉድድሩን የጨረሰችዉ 2፡27፡23 በሆነ ጊዜ ነዉ፡፡

ወንዶች

  1. ላዉረንስ ቺሮኖ(ኬኒያ) 2፡04፡06
  2. ሙሌ ዋሲሁን(ኢትዮጵያ) 2፡04፡37
  3. ሰለሞን ደቅሲሳ(ኢትዮጵያ) 2፡04፡40
  4. ጌዲዮን ኪፕኪተር(ኬኒያ) 2፡06፡15
  5. ካኣን አዝቢለን(ኬኒያ) 2፡06፡24

ሴቶች

  1. ታደለች በቀለ(ኢትዮጵያ) 2፡23፡14
  2. ሻሾ ኢንሰርሙ(ኢትዮጵያ) 2፡23፡27
  3. አዝመራ ገብሩ(ኢትዮጵያ) 2፡23፡31
  4. ደሲ ጂሳ(ኢትዮጵያ) 2፡23፡37
  5. ሌኒት ማሳይ(ኬኒያ) 2፡23፡45
Similar Posts